ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ ከዉሀ የኤልክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ካላቸዉ የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ አንደሆነች የሚታወቅ ቢሆንም ካላት 45000 ሜ.ዋ. ኤልክትሪክ የማመንጨት አቅም አገልግሎት ላይ የዋለዉ 5% የሚሆነዉ ብቻ ነዉ፡፡
የኢትየጵያ መንግስት ሀገሪቱን ለማሳደግ በሚያደርገዉ ጥረት በጊቤ ወንዝ ላይ 4,600 ሜ.ዋ. የኤልትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለዉ ግድብ እና 175,000 ሄክታር መሬት ላይ የኩራዝ ሸንኮራ ልማት ፕሮጀክት በጊቤ ተፋሰስ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የግንባታዉ ዓላማ የኃይልና የዉሀ ፍላጎትን ለሟሟላትና የሀገሪቱን ብሔራዊ ምጣኔ ሀብት ማሳደግ ነዉ፡፡
ኦሞ ቱርካና ተፋሰስ የ2018 ዓበይት ክንውኖች
1. የባለድርሻ አካላት ስብሰባ፣ አደስ አበባ ፣ የካቲት 2018
በኦሞ ተፋሰስ የመጀመሪያው የባለድርሻ አካላት ስብሰባ በየካቲት 2018 ተከናውኗል፡፡ በስብሰባው 20 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ተሣታፊዎቹም በውሃ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ከሚሠሩ ድርጅቶች የተጋበዙ ነበሩ፡፡ ስብሠባውን የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሀይል ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለ የከፈቱት ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸውም የውሃ ሀብት ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ዋነኛው ሀብት መሆኑን አስምረውበታል፡፡ የስብሠባው ተሣታፊዎቹም በኦሞ ቱርካና ተፋሰስ በውሃ፣ ሀይልና ምግብ መስተጋብር ዙሪያ በሚገኙ ዋና ዋና ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ በጥልቀት ተወያይተዋል፡፡
2. አካባባዊ የባለድርሻ አካላት ጉባኤ፡- ጅማ፣ ኢትዮጵያ፣ ህዳር 2018
የመጀመሪያው የ DAFNE ኘሮጀክት አካባቢያዊ የባለድርሻ አካላት ጉባኤ በኦሞ ቱርካና ተፋሰስ ፣ ጅማ ከተማ ውስጥ ተካሂዷል፡፡ ተሣታፊዎቹም ከመንግስ ባለስልጣናት ፣ ከውሃ አጠቃቀም ማህበራት፣ እና ከሙህራን የተውጣጡ ሲሆን በአጠቃላይ 12 ተሣታፊዎች ነበሩ፡፡ የጉባኤው ዋና ዓላማ DAFNE ኘሮጀክትን ለተሣታፊዎች ማስተዋወቅና በኦሞ ቱርካና ተፋሰስ በውሃ፣ ኃይልና ምግብ መስተጋብር ዙሪያ በሚገኙ ዋና ዋና ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ላይ መወያየት ነበር፡፡ በተሣታፊዎቹም በግብርና፣ በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ እና በኃይል ሴክተሮች የሚስተውሉትን ችግሮች
፣ ተግዳሮቶች እና ያሉቱን መልካም አጋጣሚዎችን እንዲሁም ለሚስተዋሉት ችግሮች የመፍትሔ ሃሳቦች በዝርዝር ለይተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በዕቅድ አለመመራት፣ ዝቅተኛ የኘሮጀክቶች አፈፃፀም እና የቁጥጥር ማነስ ዋና ዋና ችግሮች መሆናቸው ተለይቷል፡፡ በተጨማሪም ዝቅተኛ የመረጃ አያያዝ፣ የፖሊሲ ትግበራ አናሳነት፣ የፖሊሲ ማዕቀፍ አለመኖር እና ዝቅተኛ የፖሊሲ ማሻሻያዎች የተፋሰሱ አንገብጋቢ እና መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
3. የኦሞ ቱርካና ኢኮሲስተም ሰርቪስ ይዘት ጥናት
ይህ ጥናት በኦሞ ቱርካና ተፋሰስ ውስጥ የሚካሄዱ የልማት ስራዎች በተፋሰሱ ኢኮሲስተም ሠርቪስ ላይ ያላቸው አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ለይቷል፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ የሃይልና የመስኖ ልማት ያላቸውን መስተጋብር ለመተንተን የሚረዳ መረጃዎችን አሰባስቧል፡፡
ቀጣይ ስራዎች
1. በተፋሰስ ደረጃ የሚካሄድ የውይይት መድረክ፣ ሐምሌ 2019
DAFNE ኘሮጀክት ሁለተኛውን የውይይት መድረክ በሐምሌ 2019 ያካሂዳል፡፡ የውይይቱም ዓላማ ኘሮጀክቱ በመጀመሪያው የምክክር መድረክ በተነሱ የመነሻ ሃሳቦች ተመርኩዞ በሠራቸው ስራዎች ዙሪያ የተገኙ ውጤቶችን ለሚመለከታቸው አካላት ማካፈል ይሆናል፡፡ ተሣታፊዎቹም DAFNE ኘሮጀክት የተጠቀማቸውን መረጃን የመተንተኛ መሳሪያዎች የሚተዋወቁበትና ተጨማሪ ግብዓት /ግብረ መልስ/ የሚሰጡበት ይሆናል፡፡
20ኛው Water Net/WARFSA/GWP-SA ሲምፖዚየም
በውሃ ሃይልና ምግብ መስተጋብር አተገባበር ዙሪያ የተደረገ ልዩ ስብሰባ
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የውሃ አጠቃቀም ምርምር ተቋም ከኢትዬ-ዙሪክ እና ከዛምቢያ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በውሀ ሃይልና ምግብ መስተጋብር አተገባበር ዙሪያ በ 20ኛው Water Net/ WARFSA/GWP-SA ሲምፖዚየም ላይ ልዩ ስብሰባ ተደርጓል፡፡ ይህ ልዩ ሲምፖዚየም የተካሄደው በ DAFNE ኘሮጀክት መሪነት ነው፡፡ በስብሰባውም ላይ ከሀያ የሚበልጡ በማማከር ስራ ላይ የተሰማሩ አማካሪዎች፣ የመንግስት ድርጅቶችና በምርምር ስራው ላይ ዕውቀት ያላቸው ምሁራን ተካፍለውበታል፡፡
የዚህ ልዩ ሲምፖዚየም ተቀዳሚ ዓላማ የነበረው፡-
- በመካሄድ ላይ ስላለው የምርምር ስራ፣ ሥኬትና የተገኙ ውጤቶችን ለመገምገም እና
- የምርምር ስራውን መሬት ላይ አውርዶ ተጠቃሚዎች ጋር ለማድረስና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ስለማድረግ ውይይት ማድረግ ነበር፡፡
በስብሰባውም ወቅት ሁለት በመካሄድ ላይ ያሉ የጥናት ፅሑፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የቀረቡት ጥናቶች በደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ክልል ውስጥ በ DAFNE እና በውሀ ምርምር ኮሚሽን ድጋፍ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡በመቀጠልም በቀረቡት የጥናት ስራዎች ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ተሳታፊዎች የውሀ ሃይልና ምግብ መስተጋብር የምርምር ስራ መሬት ላይ አውርዶ ለተጠቃሚ ለማድረስ ተግባራዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው
አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም የምርምር ስራውን ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመድረስ ስለምርም ስራው ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡